ስለ…

|| ENGLISH version

የአባቴ  ቤት አለም አቀፍ  ቤተመዘክር

አላማ

ያህዌህ ንሲህ (እግዚአብሔር አላማችን ነው)  ዘፅአት 17፡15

    የዚህ ፕሮጀክት አላማ  አላማ  የሰው ልጅች የእግዚአብሄርን ፍቅር ተረድተው ጌታ እየሱስን በማመን የዘላለም ህይወት እንዲያገኙ እድሉን ማመቻቸት ነው!

ራዕይ

1ኛ. ከንግግር ባለፈ፤ ከንባብ ባለፈ በእይታ ወንጌል የሚመሰከርበት አዲስ አቀራረብ ማዘጋጀት

2ኛ. የመጽሐፉ ቅዱሳን ዋኝኛ ሃሳብ ወይም የእግዚያብሔርን የአብሮነት ፍላጎት ለሰው ዘር በሙሉ ለማሳወቅ

3ኛ. ለቤተከርስቲያን ሁለንተናዊ ድጋፍ ማድረግ

4ኛ. ክርስቲያናዊ የጋብቻ ትምህርት በተመለከተ ስልጠና መስጠት

መግቢያ

    በሃገራችን ኢትዮጵያ  ረጅም  ዘምን ያስቆጠሩ በተለይ በኦርቶዶክስ  ቤተክርስቲያን የተገነቡ ክርስቲያኒያዊ  አሻራ ያለቸው በርካታ መንፈሳዊ ስፍራዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ እነ ላሊበላን የመሳሰሉ እጅግ አስደናቂ አቢያተ ክርስቲያናት ለእምነቱ ተከታዮችም ሆነ ለማንኛውም ጎብኒ በትውልድ ሁሉ መካከል ያሳደሩት ክርስቲያዊ ተፅዕኖ  ትልቅና የከበረ  መሆኑ ዛሬም ድረስ የዘለቀ እውነት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከጠቅላላው የህዝብ ብዛት ከ25 እስከ 30 ሚሊየን ይጠጋል የሚባልለት የወንጌላዊያን አማኞች ህብረት በህብረቱ በኩል ከተለመደው የወንጌል አስተምሮና ምስክርነት  ውጪ  በቋሚነት ለትውልድ የሚተላለፍ አሻራን ለጎብኝዎች በሚመች መልኩ የተዘጋጀ አንድም ተቋም የለም፡፡ በመሆኑም የአባቴ ቤት አለም አቀፍ ቤተመዘክር ይህንን ፕሮጀክት ወቅታዊና አንገብጋቢ የወንግል ጉዳይ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሀሳቡ ሰዋዊ ሳይሆን እግዚያብሄርአዊ በመሆኑ ጊዜና ትውልድ ቆሞ አይጠብቀንምና በቶሎ መሰራት አለበት የሚል እምነት አለን፡፡

    የአባቴ ቤት አለም አቀፍ ቤተመዘክር ፕሮጀክት በዘማሪት ራሄል ሽባባው አማካኝነት ከእግዚያብሄር የተሰጠ ራዕይ ሲሆን ሁሉን ያዘጋጀ ግን የራዕዩ ባለቤት እግዚያብሄር ነው፡፡

    ዘማሪቷ የእግዚያብሄር ምህረት በዝቶላት በቤቱ ከአስራ ሶስት አመት  በዝማሬ በቃልና  በቤተክርስቲያን ቦርድ ሰብሳቢነት ጭምር ያገለገለችና በማገልገል ላይ ያለች፤ ባለ ትዳርና የሁለት ልጆች  እናት ስተሆን የአባቴ ቤት በሚል ርዕስ የወጣው የመጀመሪያው ካሴትና ጥናታዊ ዘጋቢ ፊልም የዚህ  ታላቅ ፐሮጀክት መነሻዎች  ናቸው፡፡

    የአባቴ ቤት አለም አቀፍ ቤተመዘክር  የእግዚያብሄርን ቤት ታሪካዊ አመጣጥ የሚናገር ወይም መፅሀፍ ቅዱስሚ ህንፃ ሲሆን በውሰጡ ከ21 ያላነሱ ታላልቅ ክፍሎች ያሉት በአይነትና በይዘት የተለየ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡

አስተዋፅኦ

    ፕሮጀክቱ የአፍሪካ መዲና ተብላ በምትጠራው አዲስ አበባ ከተማ የሚሰራ በተጠናቀቀ በመጀመሪያው አመት ብቻ  ከመቶ ሺህ በላይ የአገር ውስጥ ጎብኝዎችና ከሃምሳ ሺህ በላይ የውጭ አገር ጎብኝዎችን መሳብና ማስተናገድ የሚችል፡፡ ከዚህም ጋር በጎብኝዎች ልክ የእግዚያብሄር እውነት ወንጌልን የመመስከር ዕድል ይኖረናል፡፡

    ለአማኞቹ ጎብኝዎች ደግሞ በተለያየ  አቀራረቡ በሚሰጠው ምስክርነት ምክንያት ፅናትንና  በመንፈስ የውስጥ ጥንካሬ  የተሸለ መሰጠትን ይጨምራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ለመላ ቤተሰብ በሚደረግ ቅኝት ምስክርነቱ በእይታ የታገዘ በመሆኑ ወላጆች ልጆቻቸውን ወንጌልን ለማስተማር እጅግ ቀላል ያደርግላቸዋል፡፡

    እንደ አገር ደግሞ በሚስባቸው ጎብኝዎች ምክንያት የራሱ የሆነ አስተዋፅኦ በመወጣት የሚሰጠው ጠቀሜታ ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ ይህንን በማድረግ የአዲስ አበባ  ኢንደስትሪ ተብሎ በሚጠራው የቱሪዝም ዘርፍ  ውስጥ በጣም  ቁልፍ ሚና ይኖረዋል፡፡

    የአባቴ ቤት አለም አቀፍ ቤተመዘክር ፕሮጀክት የቤተመዘክር ግንባታ፤ መፅሐፍ ቅዱሳዊና ታሪካዊ ዳራ ተመስጦ ማሳያ ስራዎች እንዲሁም በዘላቂነት በሚኖረው የአስተዳደር ስራዎች ለቤተክርስቲያን ወጣቶች  ስራ ዕድል በመፍጠር  ከ100 ያህል ሰዎች እድል ይፈጥራል፡፡